
በግሪንላንድ ምርጫ ያሸነፈው ፓርቲ የትረምፕን ዕቅድ ተቃወመ
በግሪንላንድ በተካሄደው የምክር ቤት ምርጫ፣ ሀገሪቱ በሂደት ከዴንማርክ ነጻ እንድትወጣ የሚደግፈው ዴሞክራቲት ፓርቲ ያልተጠበቀ ድል ተቀዳጅቷል፡፡ የትላንት ማክሰኞው ምርጫ የተካሄደው፣ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ደሴቲቱን ለመጠቅለል ያላቸውን እቅድ ይፋ ባደረጉበት ድባብ ውስጥ ነው፡፡ ዲሞክራቲት ፓርቲ “የግዛቲቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወስኑት የግሪላንድ ነዋሪዎች ናቸው” በማለት የትረምፕን ንግግር ሲቃወም ቆይቷል፡፡ “የምርጫው ውጤት ግሪንላንድ አትሸጥም የሚለውን ግልፅ…