
ትረምፕ ከአውሮፓ በሚገቡ የአልኮል መጠጦች ላይ ከበድ ያለ ታሪፍ እንደሚጥሉ አስታወቁ
የአውሮፓ ኅብረት ከአሜሪካ በሚገባው ዊስኪ ላይ የ50 በመቶ ታሪፍ መጣሉን ተከትሎ፣ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ከአውሮፓ በሚገባው የወይን ጠጅ፣ ሻምፓኝና ሌሎች የአልኮል መጠጦች ላይ የ200 በመቶ ታሪፍ እንደሚጭኑ አስጠንቅቀዋል። የ27 ሃገራት ስብስብ የሆነውን የአውሮፓ ኅብረት “በዓለም የከፋው ታክስና ታሪፍ ጣይ” ሲሉ የገለጹት ትረምፕ፣ “እ.አ.አ በ1993 ሲመሠረት ዓላማው “ከአሜሪካ የኢኮኖሚ ጥቅም ለማግኘት ነው” ብለዋል። ባለፈው አንድ…