
ሚሳይል መስሪያ ግብአት በመጫን የተጠረጠረችው ሁለተኛ የኢራን መርከብ ከቻይና ተነሳች
ከቻይና የሚሳይል ነዳጅ መስሪያ ቁልፍ ግብአቶችን ጭናለች ተብላ በምዕራባዊያን የዜና ዘገባዎች የተጠረጠረችው ሁለተኛዋ የኢራን መርከብ ወደ ኢራን እያመራች መሆኑን የቪኦኤ ልዩ የትንታኔ ዘገባ አመልክቷል፡፡ የመርከብ እንቅስቃሴ ክትትል ድረ-ገጾች እንደሚያሳዩት የኢራን ባንዲራ የሚያውለበልበው ጃይራን የተባለው የጭነት መርከብ፣ ከቻይና ይነሳል ተብሎ ከተጠበቀበት ጊዜ ከአንድ ወር በኋላ ዘግይቶ ባለፈው ሰኞ መነሳቱ ተጠቅሷል፡፡ በጥር እና በየካቲት ዘ ፋይናንሺያል ታይምስ፣…