
የባለ ሥልጣናት መፈታት ለደቡብ ሱዳን ውጥረት መርገብ ቁልፍ ጉዳይ ነው ተባለ
የደቡብ ሱዳን መንግሥት በሀገሪቱ የተፈጠረውን ውጥረት ተከትሎ የታሰሩ ባለሥልጣናትን እንዲፈታ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) አባል ሀገራት መሪዎች ጥሪ አቅርበዋል። የኢጋድ አባል ሀገራት ይኼንኑ የደቡብ ሱዳን ግጭት አስመልክተው ረቡዕ መጋቢት 3 ቀን 2017 ዓ.ም በበይነ መረብ ባደረጉት ስብሰባ የደቡብ ሱዳን መሪዎች ውጥረቱን ለማርገብ ውይይት እንዲጀምሩም ጠይቀዋል። በደቡብ ሱዳን የጁባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር…